ተጨማሪ ማብራርያ

በመሠረቱ ዝማሬዎች የሚገመገሙት በሙያው የተካኑ ሰዎች ተመርጠው ነው፡፡ ግምገማው የሚካሄደው በሚከተሉት ዐሥርት መስፈርቶች መሠረት ነው፡-

  1. የዝማሬው ግጥም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትክክለኝነት አለው፡፡
  2. ዝማሬው ወጥ መልእክት ያለውና ዘመን ዘለቅ ጥራት ያለው ነው፡፡
  3. ዝማሬው ልብን የሚነካ፣ አእምሮን የሚመግብና መንፈሳዊ አሰላስሎን የሚያነሣሣ ነው፡፡
  4. የዝማሬው ቃላት ሥነ ጽሑፋዊ ብስለትና ሥነ ግጥማዊ ውበት አላቸው፡፡
  5. ዜማው፣ ኅብራዊነቱና ምቱ ልእቀት ባለው ሁኔታ የተሰናሰሉ ናቸው፡፡
  6. ዜማው (ሙዚቃው) አድማጩ የመዝሙሩን መልእክት እንዲያስታውስ ያግዘዋል፡፡
  7. ዜማው ከቃላቱ ጋር በሚገባ የተዋሃደ (የተስማማ) ነው፡፡
  8. የመዝሙሩ ወርጅናሌነትና አዲስ አቀራረብ (የፈጠራ ክህሎት፡፡
  9. የዘማሪው የመዘመር ተሰጥዖ ያለው መሆን፡፡
  10. የዘማሪው መንፈሳዊ ሕይወትና ጤናማ የሕይወት ምስክርነት ያለው መሆኑ፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በግምገማው ሂደት ላይ የሕዝብን አስተያየት (ግምገማ)  ለመጨመር አስበናል፡፡ ይህን የምናደርገው ሕዝቡ (የመዝሙሩ አድማጮች) ምርጫቸውን የሚያሳውቁበትን ዕድል በማዘጋጀትና በመስጠት

Related News

Mahlet Institute of Worship and Music
“Committed to Excellence in Worship and Music”

©2021 All rights reserved.